ከዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ ምህረቱ አያልቅምና / ለዘላለም ቸር ነውና የማዳን ኃይሉን ላሳየን / በክንዱ ለሚጎበኘን መልካሙን መዓዛ / በምስጋና አቅርቡለት በእልልታ ስገዱለት፤ ይህ አዝማች በየአብያተ ክርስቲያናቱ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የታወቀ አዝማች ነው። ቃሉንም ዜማውንም የደረሰው ተስፋዬ ጋቢሶ ነው። ተስፋዬ በ65 ዓ.ም. ክርስቶስን አግኝቶና ተለውጦ ዛሬ በወንጌል ሥራ እግዚአብሔርን የሚያገለግል የ24 ዓመት ወጣት ነው። ዩኒቨርሲቲ ሊያስገባው በሚችል ውጤት የ12ኛ ክፍል ትምህርቱን በ1969 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ አጠናቋል። ደብረ ዘይት ሆራ ዳር ከዛፍ ጥላ ሥር እለምለም ሣር ላይ ተቀምጠን በመዝሙር ስለሚሰጠው አገልግሎት አንዳንድ ጥያቄ ጠይቀነው ነበር።
FIXFIY © 2024